ለሁሉም ሞንትጎመሪ ጤናማ የትምህርት ቤት ምግቦች
ሞንቶጎመሪ ካውንቲ ካውንስል

ከ 2020 ጀምሮ፣ USDA የወረርሽኙ እፎይታ አካል የሆነ በተባበሩት የአሜሪካ መንግስታት ውስጥ ላሉ የሕዝብ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ሁሉን አቀፍ ነፃ የትምህርት ቤቶች ምግብ አቅርቦት ሲያደርግ ቆይቷል። ይህ በኛ ካውንቲ የሚገኙትን ጨምሮ በተማሪዎች በሚከተሉት ጉዳዮች ላይ ትልቅ ለውጥ አምጥቷል፤ ፡
በትምህርት ቤት የምገባ መርሃ-ግብሮች ላይ ያለን ተሳትፎን ማሳደግ
በትምህርት ቤት ምገባ ላይ የሚሳተፉ ተማሪዎች ላይ የሚታየውን መገለል መቀነስ
የካፊቴሪያ ሰልፎችን ማሳጠር
የሞንትጎመሪ ካውንቲ አሁን ላይ እርምጃ ካልወሰደ ይህ ሁሉ በሓምሌ 1፣ 2022 ሊያበቃ ይችላል። ሁሉን አቀፍ ነጻ የትምህርት ቤት ምግቦች እንዲኖሩ ያስቻለው አዋጅ ተፈጻሚነቱሰኔ 30 ላይ ያበቃል።
በካውንቲው ውስጥ ላሉ ትምህርት ቤቶች ሁሉን አቀፍ ነጻ የምገባ መረሃ-ግብሩን ያራዝሙ እና በካውንቲ ወይም በፌዴራል መንግሥት መረሃ-ግብር ላልተሸፈነ ለማንኛውም ትምህርት ቤት የካውንቲ የገንዘብ ድጋፍ ያድርጉ።
Sponsored by
To:
ሞንቶጎመሪ ካውንቲ ካውንስል
From:
[Your Name]
የሞንትጎመሪ ካውንስል ምክር ቤት አባላት እና የMCPS BOE፣ በመንቶጎመሪ ካውንቲ ላሉ ጤናማ የትምህርት ቤት ምግቦች ድጋፍ አሁኑኑ ለምግብ እኩልነት ሲባል ድጋፍ እንድትሰጡ አሳስባለሁ።
በሓምሌ 1, 2022 10,000 ልጆቻችን የትምህርት ቤት ምግብ ሊያጡ ነው
ለሁሉም ሞንትጎመሪ ጤናማ የትምህርት ቤት ምግቦች ማንኛውንም የትምህርት ቤት ምግብ የሚፈልግ ወይም የሚያስፈልገውን ተማሪ ወላጆቹን ምን ዓይነት ክፍያ ሳያስከፍል ይቀበላል። የፌደራል መንግስት ነጻ የትምህርት ቤት ምግብ ለማግኘት ብቁ ለመሆን የወጡ የገቢ ብቁነት መስፈርቶችን ለሁሉም ተማሪዎች በአዋጅ ሽሯል፣ ነገር ግን የእነዚህ አዋጆች ተግባራዊነት በቅርቡ ያበቃል። እነዚህ አዋጆች ለተማሪዎች ጤናማ ቁርስ እና ምሳ በትምህርት ቤት እንዲመገቡ ዋስትና ከመስጠቻውም ባሻገር በነጻ ምግቦች ላይ ያለውን መገለልንም ቀንሰዋል። የሞንትጎመሪ ካውንቲ ከወረርሽኙ እያገገመ ባለበት ወቅት፣ ሁሉም ልጆች ሁሉንም ለመማር የሚያስቹሏቸው በጣም መሠረታዊ የሆኑ ፍላጎቶቻቸውን ማግኘታቸውን እኛ ማረጋገጥ አለብን።
Healthy School Food Maryland®፣ ከ MCCPTA እና ከBlack and Brown Coalition for Educational Equity & Excellence ጋር በመተባበር፣የሞንትጎመሪ ካውንቲ ምክር ቤት በሁሉም የMCPS ትምህርት ቤቶች የሚገኝ የነጻ ትምህርት ቤት ምግብን ለፈለገ ወይም ለሚያስፈልገው ልጅ መስጠቱን እንዲቀጥል ይጠይቃል።
የፌደራል መንግስት ትምህርት ቤቶችን ለምግብ ያወጡትን ወጪ መክፈሉን ይቀጥላል፣ነገር ግን ትምህርት ቤቶች የሚከፈሉት ልጆች በትክክል ምግብ ሲወስዱ ብቻ ነው። በፌዴራል ክፍያ እና በምግብ ዋጋ መካከል ያለው ልዩነት ብቻ ነው ካውንቲው መሸፈን ያለበት። ወረርሽኙ ከመከሰቱ በፊት፣ በዋጋ እና በመገለሉ ምክንያት የተሳትፎ መጠን ዝቅተኛ ነበር። ከፍተኛ የተሳትፎ መጠን ለMCPS አጠቃላይ ከፍተኛ የፌዴራል ገቢን ያስገኛል።
ይህን ማድረግ እንችላለን። ልንገዛው እንችላለን። አሁን ኢንቨስት በማድረግ ከፍተኛ ጥራት ያለው ምግብ ማቅረብ እና ልጆቻችን የሚያስፈልጋቸውን የተመጣጠነ ምግብ እንዲያገኙ ማድረግ እንችላለን።