የታኮማ ፓርክ የቤት ኪራይ ማረጋጊያን ለመጠበቅና ለማጠናከር የቀረበ አቤቱታ

ለታኮማ ፓርክ ከተማ ከንቲባና ምክር ቤት፡

Click here to read this petition in English

Haga clic aquí para leer en español.

በአደጋ ላይ ያለው ምንድነው?

· ወደ ግማሽ የሚጠጉት የታኮማ ፓርክ ነዋሪዎች ተከራዮች ናቸው። ከእነዚህ ውስጥ ግማሽ የሚሆኑት ከቤት ኪራይ ማረጋጊያ ሕግ ተጠቃሚ ናቸው። (ሌላው ግማሽ ከህጉ ነፃ በሆኑ ሕንፃዎች ውስጥ ይኖራሉ።)

· ሕጋችን፣ በክራይ ማረጋጊያ ውስጥ ያሉ ቤቶች ላይ የሚደረገውን ዓመታዊ የክራይ ጭማሪ፣ በዋጋ ግሽበት መጠን (የሸማች ዋጋ መረጃ ጠቋሚ) ይገድበዋል። ማለትም 2.4% በዚህ ዓመት። የካውንቲው ገደብ ከእኛ ከእጥፍ በላይ ነው፣ ማለትም 5.7%።

· ከተከራዮቻችን 47% ከገብይቸው 30% ወይም 50% ለቤት ክራይ ይከፍላሉ።

· ሕጋችን ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው ብዙ ነዋሪዎች የቤት ክራዩን ተመጣጣኝ ያደርጋል። ይህም፣ ለመላው ማህበረሰባች መረጋጋትን ይፈጥራል፤ ብዙህነቱንና ደህንነቱን ይጠብቅል።

· የምክር ቤቱ ግምገማ እና የሕጋችን ማሻሻያ ማድረግ፣ የተከራዩን መብቶችና ጥቂት አማራጮች ያላቸውን ሰዎች ተመጣጣኝ የቤት ክራይ አቅርቦት ከፍ ወይም ዝቅ ሊያደርግ ይችላል።

· የክራይ መረጋግያ ሕጋችንን ማዳከም በተለይ ጭካኔ የተሞላበት ሊሆን ሲችል፣ ጸረ-ስደተኛ ዓመፅና የኢኮኖሚ ኃይሎች ደግሞ በዋናነት ነጭ ያልሆኑትን ተከራይ ህዝባችንን አደጋ ላይ ይጥላሉ።

Petition by
Joshua Blum
ነዋሪዎች Takoma Park
Sponsored by

To: ለታኮማ ፓርክ ከተማ ከንቲባና ምክር ቤት፡
From: [Your Name]

እኛ የታኮማ ፓርክ ነዋሪዎች የሆነው፣ የከተማውን የክራይ ማረጋግያ ሕግ እንደ አብይ የስኬት ታሪክ እናከብረዋለን። ይህ 46 ዓመት ያስቆጠረ ሕግ፣ የታኮማ ፓርክ ሀብታም የሆነውን የዘር፣ የብሔርና የኢኮኖሚ ብዝሃነቱን እውን አድርጓል፣ እውንነቱንም እየጠበቀ ነው። ሕጉን ለማሻሻል እያቀዳችሁ ባላችሁበት ወቅት፣

1) የተከራይን መብቶች ቅድምያ በመስጠትና፣ በተለይም ከዝቀተኛ እስከ መጠነኛ ገቢ ላላቸው ነዋሪዎች ተመጣጣኝ የቤት ክራይን በመጠበቅ፣

2) በየዓመቱ የሚፈቀደው የቤት ኪራይ ጭማሪ ከዋጋ ግሽበት መጠን (ኢንፍሌሽን) በላይ እንዳይሆን በመገደብ
ሕጉን እንድትጠብቁልንና እንድታጠናክሩልን እናሳስባለን፥።